የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊዎች የ30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ለሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አደረገ።
ethiopian airlines sale
በቅናሹ ተጠቃሚ የሚሆኑት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 20 ቀን 2021 ድረስ ትኬት የሚቆርጡና፥ ከፈረንጆቹ ጥር 1 እስከ 31 ቀን 2022 ድረስ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ የዘመቻው ተሳታፊ መንገደኞች መሆናቸውን አየር መንገዱ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት ጥሪ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ይፋ የሆነውን 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡
ለሀገራችን አናንስም በሚል ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሀገሪቱን ሰላማዊነት ለቀሪው ዓለም ለማሳየት ሲሉ ነው በዘመቻው የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ለማክበር የሚመጡት።
Ethiopian Airlines offers a 30% off for flights to Ethiopia.  The Great Ethiopian Homecoming Discount.